Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሚሊየን ሳይበልጥ እንዳልቀረ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሚሊየን ሳይበልጥ እንዳልቀረ ተነገረ፡፡

የሃገሪቱ የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ባለስልጣናት እንዳስታወቁት ከሆነ በአሜሪካ ቢያንስ 20 ሚሊየን ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሳይያዙ አልቀረም፡፡

እንደማዕከሉ ገለጻ ትክክለኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አሁን ከተነገረው በ10 እጥፍ ከፍ ሊል ይችላል፡፡

ይህ መረጃ የወጣው ቴክሳስ የእንቅስቃሴ ገደብ መላላቱን ለጊዜው እንዲቆይ ከወሰነች በኋላ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ነጥብ 4 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን 122 ሺህ 370 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.