Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በኮሮና የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ሚሊየንን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ሚሊየንን አልፏል፡፡

እንደጆን ሆፕኪንስ መረጃ እስካሁን በአገሪቱ 25 ሚሊዮን 3ሺህ 695 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፤ 417 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት አዲስ የኮሮናቫይረስ አይነት መግኘቱ የሚታወቅ ሲሆን፤ ይህም በበርካታ አገራት እየታየ ነው፡፡

በዚህም አሜሪካ ስጋት ውስጥ መሆኗ እየተነሳ ይገኛል፡፡

ሆኖም ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የክትባት ምርትን ለማስፋት ፣ ሙከራዎችን ከፍ ለማድረግ እና ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት ያተኮሩ 10 ትዕዛዞቸችን በፊርማቸው አጽድቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ወደዚህ ውጥንቅጥ ውስጥ የገባነው በአንድ ሌሊት አይደለም ፣ ከችግሩም ለመውጣት ብዙ ወራትን ይወስዳል ያሉ ሲሆን ይህን ቫይረስ እናልፈዋለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

እስከ ፈረንጆቹ ጥር 23 ቀን ድረስ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከያ ማዕከል እንዳስታወቀው ከ3 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት እየወሰዱ ነው ተብሏል ፡፡

እስካሁን በአለም አቀፍ ደረጃ ከ99 ሚሊየን 774 ሺህ በላይ ሰዎች በቫረሱ ሲያዙ፤ ከ2 ሚሊየን 139 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአንጻሩ ከ71 ሚሊየን 762 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል ፡፡

ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ብሪታንያ ከአሜሪካ ቀጥሎ የቫይረሱ ተጽዕኖ ከፍተኛ ከሆነባቸው አገራት መካከልም በቀዳሚነት የሚነሱ ናቸው፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን እና ዎርልድ ኦ ሜትር

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.