Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ታይቶ የማይታወቅ የዋጋ ጭማሪ መከሰቱን ተከትሎ ዜጎች ወደ ነጻ ምገባ ማዕከላት ለመሄድ ተገደዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የመሰረታዊ ፍጆታ እቃዎች ዋጋ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ዜጎች ወደ ነጻ ምገባ ማዕከላት እንዲሄዱ መገደዳቸው ተገልጿል፡፡

በአሜሪካ አሁን ላይ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ላይ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ በመከሰቱ በርካታ ዜጎች በአስቸጋሪ የኑሮ ጫና ውስጥ እንደሚገኙ ፎክስ ኒውስ ዘግቧል፡፡

በተፈጠረው ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ምክንያትም በርካታ ቤተሰቦች መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በመደበኛ ሱቆች መሸመት አለመቻላቸው ተመላክቷል፡፡

ይህን ተከትሎም ዜጎች መንግስት መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎችን በነጻ የሚያከፋፍልባቸውን የምገባ ማዕከላት አጨናንቀዋል ነው የተባለው፡፡

በዚህ ሳቢያም አሁን ላይ በአሜሪካ የሚገኙ 40 በመቶ የሚሆኑት የምገባ ማዕከላት የዜጎች ፍላጎታ በመጨመሩ ከፍተኛ የአቅርቦት ችግር ያጋጠማቸው መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል፡፡

የዋጋ ጭማሪው በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ተስፋ አስቆራጭ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን ÷ ሁኔታው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጊዜ ከነበረው በእጅጉ እንደሚከፋ ተጠቅሷል፡፡

በርካታ አሜሪካውያንም የዕለት ጉርሳቸውን ከወርሃዊ ገቢያቸው ጋር ለማጣጣም በመደበኛ ሱቆች አስፈላጊ የሚባሉትን የፍጆታ እቃዎች ብቻ መርጠው ለመግዛት እየተገደዱ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ለተጨማሪ እርዳታም ዜጎች መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች በነጻ ወደ ሚከፋፈልሉባቸው የመንግስት የምገባ ማዕከላት ማቅናት ግዴታ እየሆነባቸው ነው ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.