Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ መድሀኒቶችንና የህክምና ግብአቶች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ7 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር በላይ የሚያወጡ መድሀኒቶችንና የህክምና ግብአቶችን ድጋፍ አደረጉ፡፡
በሚኒሶታ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ባቀረበላቸው ጥያቄ መሰረት የሜዲካል ኤክስፕረስ ትሬዲንግ ባለቤት የሆኑት አቶ እዩኤል ዮሴፍ ዘለቀ ዳይሬክት ሪሊፍ ኢንተርናሽናል ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር መድኃኒቶችን እና ሰፕላይስ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በራሳቸው ወጭ አጉዋጉዘው የፊታችን ረቡዕ እለት አዲስ አበባ እንደሚደርስ ታውቋል፡፡
ለተደረገው ድጋፍ የቆንስላው ኃላፊ አምባሳደር አብዱልአዚዝ መሐመድ ምስጋና ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.