Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የበቃ ንቅናቄ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ፣ ሜሪላንድና ቨርጂንያ ግዛቶች የበቃ ንቅናቄ አካል የሆነ ሰልፍ ተካሄደ፡፡

በግዛቶቹ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት እና የሀሰት የሚዲያ ክስ በመቃዎም “የበቃ ” ዘመቻ አካል የሆነ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን በአሜሪካ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች አንዳንድ ምእራባውያን ሀገራት በቀጥታና በሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም በመገናኛ ብዙሃኖቻቸው በኩል በኢትዮጵያ ላይ እያደረሱት ያለውን ተፅእኖ እንዲያቆሙ የሚጠይቁ ሰልፎች በመላው ዓለም መካሄዳቸውን ቀጥለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.