Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ አደገኛ የህዝብ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ የዝንጀሮ ፈንጣጣ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ በሽታውን አደገኛ የህዝብ የጤና ስጋት መሆኑን አወጀች።

አሜሪካ እስከ ትናንትና ብቻ ከ6 ሺህ 600 በላይ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ መያዛቸውን ማረጋገጧ የተነገረ ሲሆን ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው 25 ሺህ 800 ሰዎች የ25 በመቶውን ድርሻ ይይዛል ተብሏል፡፡

የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ ጸሃፊ የሆኑት ዣቬር ቤሴራ ለጋዜጠኞች በሰጡት ገለጻ÷ የአሜሪካ መንግስት ቫይረሱን በመቆጣጠር ረገድ ቀጣይ እርምጃዎችን ለመውሰድ ዝግጅት መጨረሱን ጠቁዋል።

ሁሉም አሜሪካዊ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ቫይረስ አደገኛነትን እንዲረዳ እና አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሁሉ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝ መከሰቱን አረጋግጠው ሪፖርት ካደረጉ እና ቫይረሱን ለመከላከል የበሽታውን አደገኛነት ቀደም ብለው ካወጁት መካከል ኒውዮርክ፣ ካሊፎርኒያ እና ኢሊኖይ ቀዳሚዎቹ መሆናቸው ይታወሳል፡፡

አሁን ላይ ኒውዮርክ፣ ሳን ፍራንሲስኮን እና ሎስ አንጀለስን ጨምሮ አንዳንድ ከተሞች የራሳቸውን የበሽታውን አደገኛነት ማወጃቸውን ሺንዋ ዘግቧል።

የአሜሪካ የጤና እና የሰብዓዊ አገልግሎት መምሪያ ÷ የዝንጀሮ ፈንጣጣ ተሥፋፍቶ ብሔራዊ ሥጋት እንዳይሆን እየሠሩ መሆናቸውን ባለሥልጣናቱ አስታውቀዋልም ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.