Fana: At a Speed of Life!

በአምስት ወራት ውስጥ 147 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምስት ወራት ውስጥ 147 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፥ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ የኮሮና ወረርሽኝን፣ አገራዊ የፀጥታና መሰል ተግዳሮቶችን በመቋቋም 147 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም የእቅዱን 92 ነጥብ 69 በመቶ ማሳካት መቻሉ ተገልጿል፡፡
ገቢው ከ2ዐ13 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀርም የ20 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወይም 16 ነጥብ 27 በመቶ ዕድገት አሳይቷል ተብሏል፡፡

ገቢው የተሰበሰበው ከሀገር ውስጥ ታክስና ከውጭ ንግድ ቀረጥና ታክስ መሆኑ ታውቋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.