Fana: At a Speed of Life!

በአምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የመስኖ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ በ64 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባ የላይኛው ሚሌ መስኖ ፕሮጀክት ተመርቆ አገልግሎት ጀመረ።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገርና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ተገኝተዋል።
የክልሉ ውሃ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው በወቅቱ እንደገለጹት÷የመስኖ ፕሮጀክቱ 6 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የውሀ መውረጃ ቦይ የተገነባለትና 350 ሄክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ነው።
ፕሮጀክቱ 750 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
በዛሬው እለት የተመረቀው ፕሮጀክቱ በመስኖ ልማት ስልጠና በተሰጣቸው አርሶ አደሮች ስራ እንዲጀምር መደረጉን አስታውቀዋል።
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት 2 ሺህ 955 ሄክታር መሬት ማልማት የሚችሉ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ሃላፊው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገርና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ዛሬ ከቀትር በኋላም የይስማ ንጉስ ሙዚየምና 40 ሜትር ርዝመት ያለውን የአጅማ ድልድይ ይመርቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.