Fana: At a Speed of Life!

በአራዳ ክፍለ ከተማ ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 48 ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር በአራዳ ክፍለ ከተማ በተያዘው በጀት ዓመት ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ 48 ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸው ተገለጸ፡፡

ፕሮጀክቶቹን የአራዳ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲን ወክለው የሚወዳደሩ እጩዎች፣ የክፍለ ከተማው አመራሮች እንዲሁም የፓርቲው አባላት ጎብኝተዋል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንጂነር ያየ አማረ ÷ክፍለ ከተማው ፕሮጀክቶችን መጀመር ብቻ ሳይሆን ለማጠናቀቅ  እየሰራ ነው፡፡

በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት ከተጀመሩት 51 ፕሮጀክቶች እስካሁን 48ቱ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ቀሪዎቹ ፕሮጀክቶች እስከ በጀት ዓመቱ መገባደጃ ድረስ ይጠናቀቃሉ ብለዋል፡፡

ለአገልግሎት ዝግጁ ከሆኑ ፕሮጅክቶች መካከል በትምህርት ቤቶች የተገነቡ 22 የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሾችና  እንዲሁም የማብሰያ ቦታዎች  እንደሚገኙባቸው  ኃላፊው ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ሰባት የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች፣ የጤና ጣቢያ እድሳት፣ የወረዳ አስተዳደር ህንጻዎች እድሳትና በሶስት ትምህርት ቤቶች የተገነቡ ሶስት ዘመናዊ የመጸዳጃ ቤቶች ይገኙባቸዋል፡፡

የአራዳ ክፍለ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሚደቅሣ ከበደ በበኩላቸው÷ በፕሮጀክቶች መካከል በትምህርት ቤቶች ላይ የተገነቡት ግንባታዎች ፓርቲው ለመጪው ትውልድ ራዕይና ግብ መሳካት የሚሰራ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

ፕሮጀክቶችን በፍጥነትና በጥራት ማጠናቀቅ እንደ ባህል ተደርጎ መወሰድ አለበትም  ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.