Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞን በተከራዩ ላይ የ500 ብር የኪራይ ዋጋ የጨመረው አከራይ በ10 ሺህ ብር ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል የአርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ በተከራዩ ላይ የ500 ብር የኪራይ ዋጋ የጨመረው አከራይ በ10 ሺህ ብር ተቀጣ።

አከራዩ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመተላለፍ በተከራይ ላይ የቤት ክራይ ዋጋ በመጨሩ መቀጣቱን ከአርሲ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ የህዝብ ግንኙነት በፌስቡክ ገፁ ባሰፈረው ጽሁፍ አመልክቷል።

ግለሰቡ ግንቦት 11 2012 ዓ.ም ከጥዋቱ 4 ሰዓት ሲሆን አርሲ ዞን፣ሙኔሳ ወረዳ ቀርሳ ከተማ ውስጥ የቤቱ ተከራይ ግለሰብ በፊት ከሚከፍለው 500 ብር ላይ 500 ብር በመጨመር 1 ሺህ ብር እንዲከፍል አሊያም ከቤቱ እንዲወጣ መጠየቁን ነው መረጃው የሚያመለክተው።

አከራዩ በዚህም የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጣውን አዋጅ ተላልፎ በመገኘቱ የወረዳው ፖሊስ ጉዳዩን በማስረጃ በማስደገፍ የምርመራ መዝገቡን ለፍርድ ቤት ማቅረቡ ተገልጿል፡፡

የአርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ፍርድ ቤትም የቤት አከራዩ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ10 ሺህ ብር እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን ከአርሲ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ምክትል ኮማንደር ጎሳ አማን አስታውቅዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.