Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞን ”ኦሮሞ የሆንክ ከአሸባሪዎቹ ህወሃት እና ሸኔ ቡድኖች ጋር ጥምረት የፈጠርክ ተመለስ” የሚል ስነ ስርአት እየተካሄደ ነዉ

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ዛሬ በአርሲ ዞን ከ5 ዞኖች የተወጣጡ አባገዳዎች እና ሀደ ሲንቄዎች በተገኙበት ”ኦሮሞ የሆንክ ከአሸባሪዎቹ ህወሃት እና ሸኔ ቡድኖች ጋር ጥምረት የፈጠርክ ተመለስ (ቆረ ዋሙ) ” የሚል ስነ ስርአት እየተካሄደ ነዉ፡፡

ስነ ስርዓቱ በስህተት ወይም ባለማወቅ ሀገር የማፍረሱ ተግባር ላይ የተሰማራችሁ በሰላም ወደ እኛ ተመለሱ የሚል ነዉ።

በኦሮሞ ባህል በሲንኮ መንዶ ይህ “የቆረ ሰሙ” ጥሪ ሲደረግ ከቡድኖቹ ጋር ግንኙነት ያለዉ የቡድኖቹ አላማ አስፈፃሚ የሆኑ እና አባል የሆኑ በተደረገዉ ጥሪ በ ሰባት ቀን ዉስጥ አከባቢዉ ወጀሚገኙ አባ ገዳዎች በመሄድ ጥሪዉን መቀበላቸዉን ማሳወቅ አለባቸው ተብሏል።

ይህም በሰላም እጅ መስጠት ይሆናል ነው የተባለው።

ነገር ግን ይህን “የቆረ ሰሙ” ጥሪ ሳይቀበሉ ከአሸባሪ ቡድኖቹ ጋር ግንኙነታቸዉን የቀጡሉ እና ያልተመለሱ ቀጣይ (ጂልቢ ኢቲ ሙሩ ) በጠላትነት መፈረጅ ስነ ስርዓት ይከናወንባቸዋል ሲሉ አባገዳ ሀጂ አልይ ሱሩር ተናግረዋል።

በሊያ ዱጉማ

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.