Fana: At a Speed of Life!

በአርባምንጭ ለአንድ ሺህ ህፃናት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርባምንጭ ከተማ በተለያዩ ምክንያቶች መማር ላልቻሉ አንድ ሺህ ህፃናት የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡
ድጋፉ በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት መማር ያልቻሉ ህፃናት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የሚያግዛቸው ነው ተብሏል።
በድጋፍ መርሐ ግብሩ ላይ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የደቡብ ክልል ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ አቶ አልጋዬ ኦጆሎ፣የጋሞ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
የመማሪያ ቁሳቁሶቹን ብርቱ ተስፋ የህፃናት መርጃ ማዕከል ከለጋስ ኢትዮጵያዊያን እንዳሰባሰበ ተገልጿል።
ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ አድራጎት ተግባራት የኢትዮጵያውያን ባህል የሆነው መደጋገፍን ከማሳደጋቸውም በላይ የህዝቦችን ትስስር የማጠናከር አቅማቸው ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።
የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሀኑ ዘውዴ፥ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ከራስ ተሻግሮ የሌላውን ችግር ለመረዳት መሞከር የወንድማማችነት መገለጫ መሆኑን አንስተዋል።
“ለጋስ እጆች ለኢትዮጵያ ልጆች ” በተሰኘው የድጋፍ መርሀግብር በሀገሪቱ ውስጥ አስር ሺህ ህፃናት ተጠቃሚ ይሆናሉ።
በሞሊቶ ኤልያስ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.