Fana: At a Speed of Life!

በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጥፋተኛ የተባለው ጥላሁን ያሚ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጥፋተኛ የተባለው ጥላሁን ያሚ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡
ውሳኔውን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ተኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው፡፡
ችሎቱ ዛሬ የተሰየመው የቅጣት ውሳኔውን ለመስጠት ነው፡፡
በዚህም አንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚን በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
ሁለተኛ ተከሳሽ ከበደ ገመቹን በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነ ሲሆን ሶስተኛ ተከሳሽ አብዲ አለማየሁ ላይ የ6 ወር ቀላል እስራት ተወስኗል፡፡
በዙፋን ካሳሁን

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

በዙፋን ካሳሁን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.