Fana: At a Speed of Life!

በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 22፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም የሚካሄደው የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና እንደቀጠለ ነው፡፡

በርካታ ታዳጊ አትሌቶች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታዳጊዎች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከታህሳስ 20 2012 ዓ.ም ጀምሮ በአሰላ አረንጓዴ ስታዲየም በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች በአሎሎ ውርወራ፣ በዲስከስስ ውርወራ፣ በ400 ሜትር ሴቶችና ወንዶች በ800 ሜትር ሴቶችና ወንዶች የፍጻሜ ውድድርና በርከት ያሉ የማጣሪያ ውድድሮች ተካሂደዋል፡፡

የሁለተኛ ቀን የኢትዮጵያ ታዳጊዎች ከ16 እና 18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውሎ በዲስከ ስ እና ርዝመት ዝላይ ወንዶች በ100 ሜትር፣ በ800 ሜትር፣ በ400 ሜትር ወንዶችና ሴቶችን ጨምሮ 12 የፍጻሜና በርከት ያሉ የማጣሪያ ውድድሮች መካሄዳቸው ታውቋል፡፡

የሶስተኛ ቀን የኢትዮጵያ ታዳጊዎች ከ16 እና 18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በጦር ውርወራ እና ስሉስ ዝላይ  ወንዶች፣ በ400 ሜትር መሠናክል ሴቶች፣ በ100 ሜትር እና በ200 ሜትር መሠናክል ወንዶችና ሴቶች ውድድሮች ተደርገው ዘጠኝ የፍጻሜ ውድድሮች መካሄዳቸውን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.