Fana: At a Speed of Life!

በአሰላ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ የሚያበረታታ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ በዞኑ ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች እና ከአሰላ ከተማ የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የድጋፍ ሰልፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን፣ መላውን የለውጥ አመራር እና ብልፅግና ፓርቲን ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

“በህብር ወደ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚህ ሰልፍ የሰላም፣ የአንድነትና ፍቅር አስፈላጊነት በሰፊው ተንጸባርቋል።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.