Fana: At a Speed of Life!

በአሰቃቂ ሁኔታ ሰው የገደለው ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወንድሜን ገድሎብኛል በሚል ቂም በቀል በአሰቃቂ ሁኔታ ሰው የገደለው ግለሰብ በ21 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ፡፡
ተከሳሽ ጎዳዳው መልኬ÷ ወንድሜን ገድሎብኛል በሚል ቂም በቀል አብዩ በሪሁንን ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ5 ሰዓት ከ30 አካባቢ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ጆካ ሆቴል ውስጥ በቢለዋ የግራ ጎኑን በመውጋት እና አንገቱን ገዝግዞ በማረድ፣ ጉሮሮውን ሙሉ በሙሉ በመቁረጥ ሕይወቱ እንዲያልፍ ማድረጉን የክስ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

በዚህም በከባድ የሰው መግደል ወንጀል በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበት ክርክር ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡
ተከሳሹ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ከባድ ውንብድና እና ግድያ ወንጀል ችሎት ቀርቦ የእምነት ክህደት ቃሉን ሲጠየቅ ድርጊቱን አልፈፀምኩም በማለቱ ዐቃቤ ሕግ ያሰባሰባቸውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች በማቅረብ መከራከሩን የፍትሕ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ተከሳሽም 2 መከላከያ ምስክሮችን አቅርቦ በማሰማት የተከራከረ ቢሆንም÷ የዐቃቤ ሕግን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ በተከሰሰበት አንቀፅ ስር ጥፋተኛ ነው በማለት ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት 4 የቅጣት ማቅለያ ተይዞለት በ21 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.