Fana: At a Speed of Life!

የአስችኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ ከአሸባሪው የሕወሐት እጅ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ አወጀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 22፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአስችኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ ከአሸባሪው የሕወሐት እጅ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሰላምንና ጸጥታን ለማስፈን እንዲሁም የሕዝብንና የንብረትን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ አወጀ።
 
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዙ ዛሬ ማምሻዉን ባደረገው ስብሰባ የዐዋጁን አፈጻጸም ገምግሟል።
 
በግምገማውም አዋጁን በመፈጸም ረገድ የሕዝቡ ተነሣሽነትና ቆራጥነት የሚደነቅ በመሆኑ ምስጋና አቅርቧል። የተገኙ ድሎችን ጠብቆ ለማስቀጠል እንዲቻልም የሚከተሉትን ትእዛዞች አስተላልፏል።
 
በዚህም መሰረት፦
 
1. ከአሸባሪው የሕወሐት እጅ ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሰላምንና ጸጥታን ለማስፈን እንዲሁም የሕዝብንና የንብረትን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲባል ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የሰዓት እላፊ ታውጇል።
 
2. ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች የታወጀውን የሰዓት እላፊ በተመለከተ ወደ አካባቢው የገቡ የመንግሥት የጸጥታ አካላት ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩ፤ እንዲሁም የሰዓት እላፊውን እንዲያስፈጽሙ ትእዛዝ ተሰጥቷል።
 
3. ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡ አካባቢዎች ከመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በክልሉ መንግሥት ከሚመደብ ሲቪል አስተዳደር ጥምር ኮሚቴ በአስቸኳይ እንዲቋቋም። በዚህ ኮሚቴ አማካኝነት በአሸባሪው ወራሪ ኃይል በመንግሥት ተቋማት፣ በግለሰብ ንብረቶች፣ በማኅበራዊ ተቋማትና በመሠረተ ልማቶች ላይ የደረሰውን ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመትን የሚያሳዩ ማስረጃዎች እንዳይጠፉ እንዲጠበቁ፣ በተገቢው መንገድ እንዲመዘገቡ፣ ማስረጃዎችም እንዲሰነዱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዕዙ ትእዛዝ ሰጥቷል።
 
4. የፍትሕ አካላት በየቦታው ከተቋቋሙ ጥምር ኮሚቴዎች ማስረጃዎችን ተቀብለው በማደራጀት ለሚመለከተው አካል እንዲያስረክቡ ታዝዟል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አመልክቷል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.