Fana: At a Speed of Life!

በአስፈፃሚ አካላት የሚደርሱ አስተዳደራዊ በደሎች መፍትሄ እንዲያገኙ በማድረግ ሂደት ችግሮች እየገጠሙት መሆኑን ዕንባ ጠባቂ ተቋም ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንዳንድ አስፈፃሚ አካላት በዜጎች ላይ የሚያደርሱትን አስተዳደራዊ በደል ለማስተካከል የሚቀመጡ መፍትሔዎችን ተግባራዊ በማድረግ በኩል ችግሮች እየገጠሙት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ፡፡

ተቋም ይህንን ያስታወቀው የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ዙሪያ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትና ሌሎች ባለድርሻ አካለት ጋር በአዳማ እየመከረ በሚገኝበት ወቅት ነው ተብሏል።

የተቋሙ ዋና ዕንባ ጠባቂ ዶክተር እንዳለ ሃይሌ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት ከሁለት አዋጆች የሚመነጭ ከአዋጅ ቁጥር 1142/2011 እና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 የተሰጠው ስልጣን አለ።

በዚህም መሰረት አስፈፃሚ አካላት በዜጎች ላይ የሚያደርሱትን አስተዳደራዊ በደሎች በመመርመርና የመፍትሔ ሃሳብ በማቅረብ ተፈፃሚ እንዲሆን ማድርግ ይጠበቅበታል።

ይሁን እንጂ ተቋሙ የሚሰጣቸው የመፍትሄ ሃሳቦች በብዛት ተፈፃሚ አለመሆናቸውን ነው ያብራሩት።

በዚህም በ2012 ዓ.ም በአስፈፃሚ አካላት የደረሱ አስተዳደራዊ በደሎችን በመመርመር ያስቀመጣቸው የመፍትሄ ሃሳቦች ተፈፃሚ እንዲሆኑ በማድረግ በኩል ስኬቱ 48 በመቶ ብቻ መሆኑን አንስተዋል።

ይኸው የማስፈጸም ምጣኔ ባለፉት ስድስት ወራት ወደ 51 በመቶ ከፍ ቢልም ከሚቀርበው ችግር አንፃር አሁንም በቂ አይደለም ብለዋል።

በአስር ዓመቱ መሪ ዕቅድ መሰረት ኢተዮጵያ በአፍሪካ ሞዴል የዕንባ ጠባቂ ተቋም የመፍጠር አላማ ሰንቃለች።

ለእቅዱን ስኬታማ ለማድረግ ብዙ ስራዎች ይጠበቃሉ ያሉት ዶክተር እንዳለ ተቋሙን ከማንኛውም ፖለቲካና የመንግሥት አስፈፃሚ አካላት ተፅእኖ ነፃና ገለልተኛ ለማድረግ ሰፊ ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።

በዚህም የተቋሙ የለውጥ ስራ ነፃና ገለልተኛ እንዲሆን በሚያስችል መንገድ የተደራጀ እንደሆነ መግለጸቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ለታችኛው የህበረተሰብ ክፍል ድምጽ የመሆን ሃላፊነትን በመውሰድ የተጠያቂነትን መርህ በመከተል አስፈፃሚ አካላት በግልጽነት መስራታቸውን ይከታተላል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.