Fana: At a Speed of Life!

በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ19 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአውሮፓ ሕብረት የአስቸኳይ ጊዜ ትረስት ፈንድ እና ዓለም አቀፉ ነፍስ አድን ኮሚቴ ጋር በመተባበር ከአውሮፓ ህብረት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ከ19 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን አስመረቀ፡፡
ሆስፒታሉ ካስመረቃቸው ግንባታዎች መካከል፥ ለእናቶችና ሕጻናት አገልግሎት የሚሰጥ የማዋለጃ ሕንጻ፣ የጽንስና ማህፀን ተኝቶ ህክምና፣ የውጭ መፀዳጃ ቤቶችና ልብስ ማጠቢያዎች፣ የማጠቢያ ማሽን እንዲሁም 50 ሺህ ሊትር የሚይዝ የውሃ ማጠራቀሚያ ታንከር ይገኙበታል፡፡
ፕሮጀክቶቹን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ፣ በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ነፍስ አድን ኮሚቴ ዳይሬክተር ፍራንክ ማክማኑስ እንዲሁም የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች በተገኙበት መመረቁን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.