Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ለከፋ ሰብዓዊ ቀውስ የተጋለጡ ወገኖችን መልሶ ማቋቋም ከሁሉም ይጠበቃል – አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 23 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ለከፋ ሰብዓዊ ቀውስ የተጋለጡ ወገኖችን መልሶ ማቋቋም ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ ተናገረ።

አሸባሪ ቡድኑ ከሰሞኑ በአፋር ክልል ጭፍራ ግንባር በወገን ጦር ሽንፈት ገጥሞት ከመፈርጠጡ በፊት ንፁሃንን ጨፍጭፏል፤ ዘረፋ ፈፅሟል፤ የእምነት ተቋማትን ጨምሮ ሀብት አውድሟል።

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ በጭፍራ ከተማ በመገኘት አሸባሪ ቡድኑ ያደረሰውን ውድመት እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ጎብኝቷል።

አሸባሪው ህወሓት በከተማዋ ያደረሰው ውድመት እና ሰብዓዊ ቀውስ እጅግ አሳዛኝ እና ልብ ሰባሪ መሆኑን ኃይሌ ተናግሯል።

የሽብር ቡድኑ በወገን ጦር የተቀናጀ ማጥቃት ሽንፈት እየተከናነበ በመሸሽ ላይ እንደሚገኝ የኢዜአ ዘገባ ያመላክታል።

በቅርቡም አሸባሪ ቡድኑ በወረራ ይዟቸው የነበሩ በርካታ ቦታዎች ነፃ መውጣታቸው ይታወቃል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.