Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት ጉዳት የደረሰበት የራስ ጋይንት ንፋስ መውጫ አካባቢን መልሶ ለመገንባት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህወሓት የሽብር ቡድን ጉዳት የደረሰበት የራስ ጋይንት ንፋስ መውጫ አካባቢን መልሶ ለመገንባት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር በመካሄድ ላይ ነው፡፡

የህወሓት የሽብር ቡድን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ቆርጦ በተነሳበት ወቅት በራስ ጋይንት ንፋስ መውጫ አካባቢ ለዘጠኝ ቀናት መቆየቱ በመርሐ ግብሩ ተመላክቷል፡፡

የሽብር ቡድኑ በወረራ በቆየባቸው ቀናትም የጤና እና ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ 286 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የተለያዩ የህዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል ተብሏል።

ይህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብርም ንፋስ መውጫና ራስ ጋይንትን ወደ ቀደመ መልካቸው ከመመለስ ባለፈ የተሻለ ደረጃ ላይ የማድረስ ዕቅድ የተያዘበት መሆኑም ተገልጿል፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጥላሁን ደጀኔ፥ ዛሬ እየተከናወነ ባለው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ሀብት ከማሰባሰብ ባለፈ አካባቢውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን የማነቃቃት ስራዎች መሰራተቸውን ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለትም በ10 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ለመገንባት የመሬት ርክክብ መደረጉን ተናግረዋል ።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ የተለያዩ የግልና የመንግስት ተቋማት፣ ባለሀብቶች እና በተለያዩ ሀገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆችን ጨምሮ ከ150 ሚሊየን ብር ድጋፍን የማሰባሰብ ዕቅድ መያዙን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የገቢ ማሰባሰብ መርሐ ግብሩ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።

በፀጋዬ ወንድወሰን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.