Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪዎቹ  የህወሓትና ሸኔ  ተላላኪዎች  ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣መስከረም 25፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የሽብር ወንጀል ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በነበሩ የህወሓትና ሸኔ ተላላኪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ፖሊስ አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር አቡላ ኡቦንግ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፥ እርምጃ የተወሰደው ከአሸባሪዎቹ የጥፋት ተልዕኮ በመቀበል ክልሉን ለማተራመስ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ እራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ብሎ በሚጠራው  ቡድን አባላት ላይ ነው።

በዚህም በክልሉ የጸጥታ ኃይል ዛሬ በተወሰደው እርምጃ ሶስት የጥፋት ተላላኪው ቡድን  አባላት መገደላቸውንና ሁለት ደግሞ  በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

እነዚህ የአሸባሪዎቹ  ህወሓትና ሸኔ ተላላኪዎች  ባለፉት ሁለት ቀናት በጋምቤላ ከተማ የሽብር ወንጀል ለመፈጸም ያደረጉትን ትንኮሳ ተከትሎ በተደረገው ክትትል ዛሬ በጋምቤላና ቄለም ወለጋ አዋሳኝ አካባቢ  ተደርሶባቸው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ኮሚሽነር አቡላ  አስረድተዋል።

የጥፋት ተላላኪዎች ሲጠቀሙበት የነበሩ አምስት ክላሽንኮቭ  ጠበንጃዎችም በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ተናግረዋል።

እንደ ኮሚሽነሩ ገለፃ፥ ለጊዜው ያመለጡ ሌሎች የአሸባሪዎቹ ተላላኪዎች  በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ ነው።

አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ባደራጇቸው የጥፋት ተላላኪዎች ህዝቦችን በማጋጨት ክልሉ ለማተራመስ ቢያሰቡም በህብረተሰቡና  ጸጥታ አካላት የተቀናጀ ጥረት እየከሸፈ መሆኑን ኮሚሽነር አቡላ አስታውቀዋል።

በቀጣይም ህዝቡ የሽባሪዎችን ተላላኪዎች  የጥፋት ሴራ በማምከን ረገድ የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.