Fana: At a Speed of Life!

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ለ51 ሺህ ተማሪዎች የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ፅህፈት ቤት ከተማሪዎች ምገባ ኤጀንሲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ጋር በክፍለ ከተማው ለሚማሩ ለ51 ሺህ 100 ተማሪዎች የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ አበርክተዋል።
በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች ቦርሳ፣ የደንብ ልብስ፣ ደብተር፣ እስኪርቢቶ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እና የተማሪ ጫማዎችን በየትምህርት ቤቶች የማዳረስ ተግባራት በይፋ ተጀምሯል።
በትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ለመቀነስ ለተማሪዎችና አስተማሪዎች የንፅህና አገልግሎት መስጫ ጣቢያ ግንባታዎችን ጨምሮ የንፅህና መጠበቂያ ግብዓቶች የማሟላት ስራዎች እና በአንድ ክፍል የ23 ተማሪ ጥምርታን ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል
https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.