Fana: At a Speed of Life!

በአትሌቲክሱ የተገኘውን ድል በሌሎችም በመድገም የጋራ ሀገርን ለመገንባት ልንጠቀምበት ይገባል- ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአትሌቲክሱ ዘርፍ የተገኘውን ድል በሌሎች ዘርፎች በመድገም የጋራ ሀገርን ለመገንባት ልንጠቀምበት ይገባል ሲል ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ገለጸ፡፡

በአሜሪካ ኦሪገን በመካሄድ ላይ ባለውየአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ከዓለም ቁንጮ መቀመጧን ያነሳው ሀይሌ ድሉ ኢትዮጵያውያንን ያለልዩነት ያስደሰተ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በመያዝ በተደጋጋሚ ድል ማድረጋቸውን በማንሳትም ይሄንን የአሸናፊነት መንፈስ በሌሎች ዘርፎችም መተግበር እንደሚገባ አንስቷል፡፡

አትሌት ሀይሌ ፥ የድሉ ምስጢር የጋራ ስራ መሆኑን በመጥቀስ ይሄንን በጋራ ሰርቶ በጋራ ማሸነፍን መለማመድ እንደሚገባ ነው የጠቀሰው፡፡

ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ የበላይነት ካላቸው ሀገራት በላይ በሻምፒዮናው መቀመጥ መቻሏን በመጥቀስ ፥ በሌሎች ዘርፎችም ውጤታማ ለመሆን በጋራ መስራት ይገባል ብሏል፡፡

ስፖርት ለሰላምና ለወንድማማችነት ያለውን ጠቀሜታ በመጠቀም ችግሮችን ለመፍታት አንዱ መንገድ አድርጎ መጠቀም እንደሚገባም ተናግሯል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.