Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አደም ፋራህ የተመራው የከፍተኛ አመራሮች ልዑክ የገርጂ መኖሪያ መንደርን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፍራህ የተመራው የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤትና የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ትናንት የተመረቀውን የገርጂ መኖሪያ መንደር ጎበኘ ።

አመራሮቹ በገርጂ የመኖሪያ መንደር የኮርፖሬሽኑን መሪዎች የፕሮጀክት አመራር ብቃትና ዘመናዊ የግንባታ ቴክኖሎጂን አስፈላጊነት አይተንበታል ያሉ ሲሆን ፥ ኮርፖሬሽኑ እየሄደበት ያለውን ፍጥነት ማስጠበቅ ከተቻለ በከተሞች ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት መፍታት እንደሚቻል በተግባር ማየታቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል የሚችሉ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማከናወን እንደሚቻል ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ልምድ መውሰድ እንደሚገባም መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡

በተለይ ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ በጥራትና በቅልጥፍና በመገንባት ያላቀ የአመራር ብቃት ካሳየው ከኮርፖሬሽኑ አመራር ልምድ መውሰዳቸውን ነው አመራሮቹ የጠቆሙት።

ፕሮጀክቱ በመዲናዋ ያለውን የመኖሪያ ቤት እጥረት በመቅረፍ ረገድ ያለው ፋይዳ የጎላ እንደሚሆንም ያላቸው እምነት ገልጸዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ወደ የአካባቢያቸው ሲመለሱ በጉብኝቱ ያገኙትን ልምድ በማካፈል መንግስት የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙም አረጋግጠዋል፡፡

ይህን አገራዊ ፋይዳ ያለውን ውጤት እያስመዘገቡ ያሉትን የኮርፖሬሽኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የማኔጅመንት አባላትና መላው ሰራተኛን ማመስገናቸውንም ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.