Fana: At a Speed of Life!

በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር በደረሰ የትራፊክ አዳጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ፋግታ ለኮማ ወረዳ ትናንት በደረሰ የትራፊክ አዳጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።
በጽህፈት ቤቱ የመንገድ ደህንነትና ትራፊክ ቁጥጥር የስራ ሂደት ቡድን መሪ ኢንስፔክተር ለዓለም ጥላሁን እንደገለፁት÷ የትራፊክ አዳጋው ከአዲስ ቅዳም ወደ አዲስ አበባ ከሰል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኤፌሰር የጭነት መኪና ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ የተከሰተ ነው፡፡
በዚህም ኤፌሰር የጭነት መኪና ውስጥ የነበሩ ሁለቱ ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በ2 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እና በንብረት ላይም ውድመት መድረሱን አስረድተዋል።
ሌሎች ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም ህክምና ተደርጎላቸው ወደቤታቸው መመለሳቸውን ገልፀዋል፡፡
አሽከርካሪዎች ፍጥነታቸውን ቀንሰው በማሽከርከር በሰውና ንብረት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ሊከላከሉ እንደሚገባም የቡድን መሪው ማሳሰባቸውን ከፋግታ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.