Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ሀገራት የኮቪድ-19 በሽታ ማገርሸቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ሀገራት የኮቪድ- 19 ወረርሽኝ ማገርሸቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡

በአውሮፓ ሀገራት በኮቪድ 19 ቫይረስ ተይዘው ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥርም ከ2 ሚሊየን መሻገሩን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

የብሪታንያ ስታትስቲክስ ቢሮ ÷ በዚህ ዓመት ከፈረንጆቹ ግንቦት 1 ጀምሮ በብሪታንያ በኮቪድ 19 የሚያዙ ሰዎች ከሕመሙ ከማገገም ይልቅ ሲጠናባቸው እንደተስተዋለ ይፋ ማድረጉን ሲጂቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የጠና የኮቪድ 19 ሕመም በታማሚዎች ላይ የትንፋሽ ማጠር ከማስከተሉም በላይ የአእምሮ መታወክ እና የመድከም ስሜት እንደሚያሳይም የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በፈረንጆቹ ግንቦት 6 ፣ 2022 ባወጣው መረጃ በ2021 መጨረሻ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበ የሞት አሃዝ ውስጥ 15 ሚሊየን ያህሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የተመዘገበ ነው ማለቱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.