Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ባየር ሙኒክ ሲያሸንፍ ሪያል ማድሪድ አቻ ተለያይቷል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር የምድብ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት በተለያዩ ከተሞች ተካሄደዋል፡፡

በምድብ አንድ ከሜዳው ውጭ ከሎኮሞቲቭ ሞስኮ የተጫወተው ባየር ሙኒክ 2 ለ 1 ሲያሸንፍ አትሌቲኮ ማድሪድ ሳልዝበርግን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡

በምድብ ሁለት የተደረጉ ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል፡፡

ሻካታር ከኢንተር ሚላን ያለምንም ጎል እንዲሁም ቦሩሲያ ሞንቼግላድባህ ከሪያል ማድሪድ 2 አቻ ጨዋታቸውን አጠናቀዋል፡፡

በምድብ ሶስት ፖርቶ ኦሊምፒያኮስን 2 ለ 0 እንዲሁም ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጭ ማርሴይን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል፡፡

በምድብ አራት ደግሞ አታላንታ ከአያክስ ያደረጉት ጨዋታ ሁለት አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

በሜዳው ሚዲቲላንድን ያስተናገደው ሊቨርፑል ደግሞ 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ከምድብ አምስት እስከ ስምንት የሚገኙ ቡድኖች ደግሞ ዛሬ ምሽት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.