Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ የዘለቀው የጋዝ አቅርቦት ቀውስ ከ“ድጡ” ወደ “ማጡ” እየሄደ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ የዘለቀው የኃይል አቅርቦት ቀውስ ከመሻሻል ይልቅ ከ”ድጡ” ወደ “ማጡ” እየሄደ መሆኑን የአሜሪካን ባንክ ጠቅሶ አንድ ግብይት ላይ መረጃዎችን የሚያወጣ ድረ-ገጽ አስነብቧል፡፡

የሩሲያ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦዎች በመበላሸታቸው ምክንያት ካለፈው ወር ወዲህ በወጪ ንግድ ወደ ሀገራቱ የምትልከውን የጋዝ አቅርቦት መቀነሷ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

ይህን ተከትሎም በአሁን ሰዓት ሩሲያ በ “ኖርድ 1” የነዳጅ ማስተላለፊያ መሥመር ብቻ ማቅረብ ካለባት የነዳጅ መጠን 20 በመቶ ያህሉን ብቻ ነዳጅ ወደ አውሮፓ ሀገራት እየላከች መሆኑ ተገልጿል፡፡

በሐምሌ ወር የነዳጅ ማስተላለፊያው መሥመር ለ10 ቀናት ለጥገና የተዘጋ ሲሆን በዚህ ሳቢያ አብዛኞቹ የአውሮፓ ሀገራት ጋዝ ሊጨርሱ እንደሚችሉ ነው እየተነገረ ያለው፡፡

በዚህ ዓመትም በአውሮፓ የነዳጅ ዋጋ በአራት እጥፍ መጨመሩን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ኅብረቱ በአቅርቦት ላይ ከተከሰተው አዘቅት ለመውጣት ወደ ኖርዌይ፣ አልጄሪያ እና አዘርባጃን በማማተር ከሩሲያ ውጪ እንዲገዙ በተፈቀደላቸው የነዳጅ መጠን መሠረት በመግዛት እጥረቱን በተወሰነ ደረጃ መፍታት ችለዋልም ነው የተባለው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.