Fana: At a Speed of Life!

በአዲሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ዳግም ምዝገባ ያላደረጉ ድርጅቶች ይዘጋሉ-ኤጀንሲው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 26 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲሱ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዓዋጅ መሰረት ዳግም ምዝገባ ያላደረጉ ድርጅቶችን እንደሚዘጋ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ገለጸ።

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ድርጅቶቹ በሚያጋጥሟቸው ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ ዛሬ መክሯል።

የኤጀንሲው የምዝገባ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ተሾመ ወርቁ በዚሁ ወቅት እንዳመለከቱት ዳግም ምዝገባ ያላከናወኑ ድርጅቶች ይዘጋሉ።

የተሻሻለው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዓዋጅ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዓዋጁ በጸደቀ በአንድ ዓመት ውስጥ ዳግም መመዝገብ እንዳለባቸው ይደነግጋል።

ድርጅቶቹ ምዝገባው ከመጠናቀቁ በፊት በመገናኛ አውታሮች ጥሪ ቢቀርብላቸውም  ምዝገባቸውን አላጠናቀቁም ብለዋል።

በኢትዮጵያ ተመዝግበው ከሚንቀሳቀሱ ከ3 ሺህ 500በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ ዳግም የተመዘገቡት 1 ሺህ 792 ናቸው ብለዋል።

መረጃ እንዳልደረሳቸው አሳውቀው ቀኑ ካለፈ በኋላ ያመለከቱ ከ50 በላይ ድርጅቶች ለዳግም ምዝገባ አመልክተው ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን አቶ ተሾመ ጠቁመዋል።

ቀሪዎቹ ዳግም ምዝገባ ከመጠናቀቁ ሁለት ወራት በፊት በተለያዩ መገናኛ አውታሮች ጥሪ ቢደረግም እንዳልተመዘገቡ ተናግረዋል።

የዳግም ምዝገባው ጊዜው መጋቢት 4 ቀን 2012 በመጠናቀቁ በዓዋጁ መሰረት ዳግም ያልተመዘገቡ ድርጅቶች እንደፈረሱ ይቆጠራል።

በመሆኑም ዳግም ያልተመዘገቡ ድርጅቶች ንብረታቸውን በማጥራት አንድ የሲቪል ማህበረሰብ ሲፈርስ ንብረቱን በጨረታ ወይንም አቅም ለሌለው ድርጅት እንደሚተላለፍም አስታውቀዋል።

ይህንንን በማድረግ በዓዋጁ እንደሚዘጉ  በመደንገጉ ይዘጋሉ ብለዋል።

በሌላ በኩል ዓዋጁ ተግባራዊ ከተደረገ በኋላ ከ800በላይ አዳዲስ ድርጅቶች ሕጋዊ ፈቃድ አግኝተው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

የኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ÷ መመዝገብና እውቅና ማግኘት ብቻ ሳይሆን፤ድርጅቶቹ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ  ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.