Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባና ጉራጌ ዞን የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች በደሴ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአዲስ አበባና ከጉራጌ ዞን አብሸጌ ወረዳ የሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ደሴ ከተማ ለሚገኙ ወገኖች ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረጉ፡፡
ድጋፉ ከሰሜን ወሎና ከአፋር ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ሲሆን÷ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት 590 ኩንታል በቆሎ እና አልባሳት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የድጋፉ አሰተባባሪዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ በአሸባሪው የህወሓት ቡድ ምክንያት ከሰሜን ወሎና አካባቢው ለተናፈቀሉ ወገኖች የሚውል የአዋቂዎችና የህጻናት አልባሳትን በማሰባሰብ አምጥተናል ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በችግር ጊዜ መረዳዳትና ለሀገራችን ክብር በጋራ መቆም ባህላችን ነውም ነው ያሉት፡፡
በመጠለያ ያሉትን ወገኖቻችንን አይተንና ሀዘናቸውን መጋራታችን ለቀጣይ ድጋፋን ለማስተባበር ትኩረት እንድንሰጥ አድርጎናልም ብለዋል፡፡
የደሴ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ሠይድ የሱፍ ከተደረገው ድጋፍ ባሻገር የጠነከረ ኢትዮጵያዊነትን ከእናንተ አይተናል በማለት በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
መላው ኢትዮጵያውያንም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል ከንቲባው፡፡
በአለባቸው አባተ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.