Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 577 ደረሰ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 2 ሺህ 577 መድረሱን የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አስታወቀ።

ቢሮው በፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ የላቦራቶሪ ምርመራ 98 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ገልጿል።

ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተገናኘም በህክምና ማዕከል ውስጥ ህክምና ሲከታተል የነበረ የ19 አመት ወጣት ህይወቱ ማለፉንም አስታውቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በትናንትናው እለት 31 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከኮሮና ቫይረስ አገግመዋል ነው ያለው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.