Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በግለሰብ ቤት የተከማቸ ከ2 ሚሊየን በላይ አዲሱ የብር ኖት ተያዘ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 12 ፣2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በግለሰብ ቤት ውስጥ የተከማቸ ከ2 ሚሊየን በላይ አዲሱ የብር ኖት መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ዶምቦስኮ ትምህርት ቤት አካባቢ በግለሰብ ቤት ውስጥ የተከማቸ ገንዘብ ስለመኖሩ ህብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው መረጃ መሠረት መያዙ ተገልጿል።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርመራ ቡድን ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ይርጋ ተካ እንደገለፁት ÷ በህዝብ ጥቆማ የተያዘው 2 ሚሊየን 222 ሺህ አዲሱ የብር ኖት የተያዘው የብሄራዊ ባንክ መመሪያን በመተላለፍ በግለሰብ እጅ እንዲኖር ከሚፈቀደው በላይ ሆኖ በመገኘቱ ነው።

ህብረተሰቡ የገንዘብ ዝውውር መመሪያውን በመተግበር ተባባሪ እንዲሆን እና መመሪያውን በመተላለፍ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን እንዲጠቁም ጥሪ ማቅረባቸውንም ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታቂ የገንዘብ ዝውውርን አስመልክቶ የባንክ አዋጅ 591/2008 እንደሚያስረዳው በአንድ ግለሰብ እጅ መገኘት ያለበት የብር መጠን 1ነጥብ 5 ሚሊየን እና ከዚያ በታች ሲሆን ይህንን ተላልፎ ከተጠቀሰው የብር መጠን በላይ ይዞ የተገኘ ግለሰብ ገንዘቡ እንደሚወረስ በግልጽ ተቀምጧል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.