Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል የፓን አፍሪካ ኮንቬንሽን ማዕከል መገንባት የሚያስችል ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ኤግዚቪሽን ማዕከል በ22 ሄክታር መሬት ላይ የፓን አፍሪካ ኮንቬንሽንና ኤግዚቪሽን ማዕከል መገንባት የሚያስችል የምክክር መድረክ ተካሄደ።

ማዕከሉ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶችን በማሳተፍ ለመገንባት የታሰበ ሲሆን፥ በምክክር መድረኩ ላይ ከ300 በላይ ኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ የአዲስ አበባን ዓለም አቀፍ ከተማነት የሚመጥንና ሁሉንም የንግድ ዘርፎች የያዘ የንግድና የኢንቨስትመንት መንደር የመገንባት እቅድ አለው ብለዋል።

በተለይም ከኢትዮጵያውያን ባለሃብቶች ጋር በመቀናጀት ከተማዋን በሚመጥን መልኩ የንግድ፣ የኮንቬንሽን እና የኤግዚቪሽን መንደር የመገንባት ፍላጎት እንዳለውም ተናግረዋል።

ባለሃብቶችም የፕሮጀክቱን ሃሳብ በመቀበል እና በማዳበር በራስ አቅም አዲስ አበባን የሚመጥን የኮንቬንሽን እና የኤግዚቪሽን ማዕከል በመገንባት እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።

ከዚህ ባለፈም የውጭ ባለሃብቶችን በመሳብ ለከተማዋ እና ለሃገራችን ተጨማሪ የስራ፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲፈጥሩ ጥሪ ማቅረባቸውን ከከንቲባ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.