Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ለደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች የግብር  መክፈያ ጊዜ ለ5 ቀን ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ1፣2012 ( ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የደረጃ ” ሐ ” ግብር ከፋዮች የግብር  መክፈያ ጊዜን ለ5 ቀን ማራዘሙን አስታወቀ።

ከሐምሌ አንድ ጀምሮ 278  ሺህ 152 ግብር ከፋዮች ለማስተናገድ ዕቅድ ተይዞ 203 ሺህ 920 ማስተናገድ መቻሉን የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጂ 75 ሺህ ግብር ከፋዮች እንደሚቀሩ ጠቅሰው እነሱን ለማስተናገድ የግብ መክፈያ ጊዜው ለአምስት ተጨማሪ ቀናት መራዘሙንም ነው የተናገሩት፡፡

አያይዘውም በዚህ ወቅት ግብራቸውን የማይከፍሉ ግብር ከፋዮች ቅጣት ይጠብቃቸዋልም ብለዋል።

እስካሁንም የደረጃ “ሐ እና ለ” 220 ሺህ 663 ግብር ከፋዮች መስተናገዳቸው ታውቋል፡፡

እንዲሁም በኮቪድ 19 ምክንያት መጨናነቅን ለማስቀረት በርካታ የጥንቃቄ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡

ቫይረሱን ለመከላከልም ሁሉም ግብር ከፋይ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና መጨናነቅን ለማሰቀረት በወቅቱ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.