Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ ለ500 ሺህ ተማሪዎች የልደት ሰርተፍኬት ሊሰጥ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 1፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ መረጃ ኤጀንሲ በመዲናዋ ለ500 ሺህ ተማሪዎች የልደት ሰርተፍኬት ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

በኢትዮጵያ ከ1952 ዓ.ም ጀምሮ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የፍትሃብሄር አካል አድርጎ ያስቀመጠው ቢሆንም፤ ህጉ ከ50 ዓመታት በላይ ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል።

የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ታከለ ነጫ ለተማሪዎቹ ሰርተፊኬቱን ለመስጠት ዝግጅቱ ተጠናቋል።

በዚህም ኤጀንሲው ሰርተፍኬቱን ለመስጠት ከከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

የትምህርት ቤቶች ርዕሳነ መምህራንም ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል ብለዋል ።

የልደት ሰርተፍኬቱን ለመስጠት ምዝገባ በኮልፌ፣ በአዲስ ከተማ እና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች መጀመሩን የገለጹት ዶክተር ታከለ በሌሎች  ክፍለ ከተሞችም ይቀጥላል ብለዋል።

ምዝገባው የዘመናዊነት መገለጫ መሆኑን ያስረዱት ዶክተር ታከለ፣ በመስኩ የሚታየውን የግንዛቤ ጉድለት ለማስተካከል እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ምዝገባው በቀጣይ በሴቶች ማህበራት፤በፖሊስና በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በዘመቻ መልክ እንደሚከናወንም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.