Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 29 ሚሊየን ብር የሚገመት በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጎርፍ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች 29 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ በገንዘብ እና በአይነት ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ከተማ አስተዳደር በጀት፣ የብልጽግና ወጣቶች ሊግ፣ በጎፍቃደኞች እና አሚባራ ኃ.የ.ግ.ማ የተሰበሰበ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

በዚህም በአፋር ክልል በጎርፍ ለተጎዱ 12 ሚሊየን ፣ በኦሮሚያ 8 ሚሊየን ፣ ለአማራ ክልል 5 ሚሊየን እና ለደቡብ ክልል 4 ሚሊየን ድጋፍ ተደርጎላቸዋል።

ምክትል ከንቲባዋ የማሰባሰብ ስራው ላይ ለተሳተፉት በጎ አድራጊ ወጣቶች፣ አሚባራ ኃ.የ.ግ.ማ እና ለብልጽግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ ምስጋና አቅርበዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.