Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከ2 ሺህ 300 በላይ ተገጣጣሚ የመማሪያ ክፍሎች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ለ2013 የትምህርት ዘመን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተገጣጣሚ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች እንደሚገነቡ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

መንግስት ዓለም አቀፉ የጤና ድርጅትና ጤና ሚኒስቴር ባስቀመጡት ምክር ሃሳብ መሰረት ኮቪድን መከላከል ማዕከል ባደረገ መልኩ ትምህርት ለማስጀመር መወሰኑ ይታወቃል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ ትምህርት ለመጀመር ግብረ ሃይል ተቋቁሞ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ ለኢዜአ ገልጸዋል።

በዝግጅቱ የመማሪያ ክፍሎችን የማፅዳት ሥራ እየተከናወነ ሲሆን ከ2 ሺህ 300 በላይ ተገጣጣሚ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችም ይገነባሉ ብለዋል።

ቀደም ብሎ ትምህርት በመቋረጡ ትምህርት ቤቶች ለተለያዩ ተግባራት በmዋላቸው ለመማር ማስተማሩ ስራ ምቹ እንዲሆኑ እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ እስካሁን ከ400 ሺህ በላይ ተማሪዎች ትምህርት ለመጀመር የተመዘገቡ ሲሆን የተጠቀሰውን ቁጥር ያህል ደግሞ ይመዘገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወላጆችም ልጆቻቸውን በማስመዝገብ ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ አቶ አዲሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከ30 ሚሊየን በላይ ዜጎች በትምህርት ላይ ቢሆኑም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከ7 ወራት በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.