Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መንደር በ93 ሄክታር መሬት ላይ ሊገነባ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽኅፈት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ክፍለ ከተማ ዘመናዊ (ስማርት) የኢንዱስትሪ መንደር በ93 ሄክታር መሬት ላይ ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ፡፡

በዘንድሮው ዓመት በ42 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት ላይ የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታውን ለመጀመር የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎችን በማጠናቀቅ ወደ ተግባር እየተገባ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር ዓባይ ከአዲስ ልሳን ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጠቁመዋል፡፡

ፕሮጀክቱ የከተማው አስተዳደር ግዙፍ የልማት ዕቅዶች አካል ሲሆን የኢንተርፕራይዞች የሽግግር ማሳለጫ በመሆንም ለከተማዋ ጉልህ ጠቀሜታ ለማበርከት ታልሞ እንደሚሠራ ተገልጿል፡፡

እስካሁን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ መንግስት የሚተዳደሩ የኢንዱስትሪ መንደሮች እንጂ መዲናዋ የራሷ የኢንዱስትሪ ከተማ እንዳልነበራት ያስታወሱት ምክትል ከንቲባ አቶ ዣንጥራር ዓባይ ፣ ከዚህ በኋላ አዲስ አበባ በክላስተር የለሙና ሼድ የተገነባላቸው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ይኖራታል ማለታቸውን ከአስተዳደሩ ከንቲባ ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.