Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሚገኙ ባንኮች ተማሪዎችን ከማገዝ ጀምሮ የከተማዋን ልማት ለመደገፍ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 28 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ ባንኮች ተማሪዎችን ከማገዝ ጀምሮ የከተማዋን ልማት ለመደገፍ ቃል ገብተዋል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመጪው የትምህርት ዘመን ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት ድጋፍን በተመለከተ ከተለያዩ የባንክ የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ÷ የከተማዋን ኢኮኖሚ በማንቀሳቀስ እና ገጽታዋን በመቀየር ረገድ የግል እና የመንግስት ባንኮች እንዲሁም የፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሆነ ተናግረዋል።

የተማሪዎች ምገባን ጨምሮ ሌሎች የተጀመሩ ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎችን እንዲደግፉም ወይዘሮ አዳነችጥሪ አቅርበዋል ።

የባንክ ሀላፊዎቹም በበኩላቸው ÷ ተማሪዎችን ለመደገፍ ባለፉት ዓመታት የከተማ አስተዳደሩን ጥሪ በመቀበል ከደብተር ጀምሮ ሌሎች ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ማለታቸውንከከንቲባ ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

በባለፈው ማክሰኞ ከተማ አስተዳደሩ ‘አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ’ በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ እና ቃልኪዳን ማስገቢያ መርሃ ግብር ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ለ20 ሺህ ተማሪዎች ጫማ ለመለገስ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.