Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሚገኙ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ለ20 ሺህ ተማሪዎች ጫማ ለመለገስ ቃል ገቡ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 27 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ለ20 ሺህ ተማሪዎች ጫማ ለመለገስ ቃል ገብተዋል።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የስፖርት ማህበረሰብ አባላት ‘አንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ’ በሚል ባዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ እና ቃልኪዳን ማስገቢያ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተዋል።

የስፖርት ቤተሰቡ በእለቱ ብቻ 8 ሚሊየን ብር የሚገመት 20 ሺህ የሚሆኑ ተማሪዎችን ጫማ ለማጨመት ቃል ገብተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመርሃ ግብሩ ላይ÷የከተማ አስተዳደሩ ላቀረበው የአንድ ጫማ ለአንድ ተማሪ መርሃ ግብር የስፖርት ማህበረሰብ ለሰጠው ፈጣን ምላሽ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ከተባበርን ፣ በጋራ ከሰራን እና አብረን ከቆምን የማናልፈው አንዳች ፈተና የለም ያሉት ወይዘሮ አዳነች የከተማ አስተዳደሩ ለሁሉም የሆነች አዲስ አበባን ለመገንባት ይሰራልም ነው ያሉት ፡፡

የስፖርት ቤተሰቡ አባላትም በበኩላቸው ÷በቀጣይነትም የከተማ አስተዳደሩ በሚያደርጋቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት ላይ ተሳትፎ በማድረግ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.