Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተመርቀዋል።
24 የመንገድ ፕሮጀክቶቹ በድምሩ 37 ነጥብ 6 ኪሜ በላይ ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ከ6 እስከ 40 ሜትር የጐን ስፋት ያላቸው እና በድምሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነቡ የተለያዩ የመንገድ ፕሮጀክቶችን በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተመርቀዋል።
በፕሮጅክቶቹ ምረቃው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ዘርፈሽዋል ንጉሴ ፣በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተግኝተዋል።
በዛሬው ዕለት የተመረቁት መንገዶች የትራፊክ መጨናነቅ ከማቃለል ባሻገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱን በማፋጠን በኩል ከፍተኛ ሚና እንደሚኖርባቸው ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
መንገዶች በራስ አቅም የተገነቡ መሆናቸውን የገለፁት ወ/ሮ አዳነች፥ ደረጃቸውን የጠበቁ መንገዶች ለመገንባት እየሰራን ሲሆን ከዚህ በላይ ለመስራት እንተጋለን ማለታቸው ከከተማው ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
24 የመንገድ ፕሮጀክቶቹ በድምሩ 37 ነጥብ 6 ኪሜ በላይ ርዝመትና የእግረኛ መንገድን ጨምሮ ከ6 እስከ 40 ሜትር የጐን ስፋት ያላቸው እና በድምሩ ከሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ወጥቶባቸዋል።
በዛሬው ዕለት በይፋ የተመረቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች ከመገናኛ – ወረዳ 17 ጤና ጣቢያ፣ ቦሌ ወረዳ 12 – ቡልቡላ 40/60 ኮንዶሚኒየም እና ሽሮ ሜዳ – ሀመረ ኖህ ኪዳነምህረት የመንገድ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.