Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የአውሮፕላን በረራዎችን አስተጓጎለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዛሬው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ሳቢያ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ሊያርፉ የነበሩ አውሮፕላኖች በሌሎች የአውሮፕላን ማረፊያዎች እንዲያርፉ ተደረገ።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፥ አብዛኛው የከተማዋ ክፍልም በጉም ተሸፍኖ ነው የዋለው።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ የአውሮፕላን በረራዎችን በማስተጓጎል ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባወጣው መረጃም፥ “ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተከሰተው ጭጋጋማ የአየር ሁኔታ አውሮፕላኖቻችን በአቅራቢያ ወደሚገኙ የአየር ማረፊያዎች ተመልሰው እንዲያርፉ ተደርጓል” ብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዚሕ ምክንያት ለተከሰተው መጉላላት ይቅርታ በመጠየቅም፤ ሁኔታውን እየተከታተለ ተጨማሪ መረጃ የሚሰጥ መሆኑንም ገልጿል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.