Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የተከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ካለፉት አመታት አንፃር በደማቅ ስነ-ስርአት ተከናውኗል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተከበረው የዘንድሮው የኢሬቻ በአል ካለፉት አመታት አንፃር በደማቅ ስነ-ስርአት መከናወኑን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።

ከንቲባዋ በአሉ በሰላም መጠናቀቁን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።

ከ150 አመት በኋላ በአዲስ አበባ እየተከበረ የሚገኘው የኢሬቻ በአል ባለፉት 3 አመታት ጀምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየደመቀ መምጣቱንም ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አንስተዋል።

በአዲስ አበባ ከ3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በአሉን በደማቅ ስነ-ስርአት ማክበራቸውንም ነው ከንቲባዋ የገለፁት።
በመዲናዋ በአሉ ሳምንቱን ሙሉ በተለያዩ ስነ-ስርአቶች ሲከበር እንደነበርም አንስተዋል።
የአዲስ አበባ ህዝብ የኦሮሞ ወገኖቹን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ያሳየው ድጋፍ እና ፍቅር በመልካም ምሳሌነቱ የሚነገርለት ነው ብለዋል ወይዘሮ አዳነች አቤቤ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.