Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፅህፈት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ሲያዘጋጁ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሰውን መረጃ መሰረት አድርጎ ባደረገው ክትትል 8 የተለያዩ መንግስት እና የግል መስሪያ ቤቶች ክብ ማህተብ፣ 2 የፌደራል ፖሊስ ፎረንሲክ የውጤት ማስረጃ፣ 8 የትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ፣ ስድስት የ8ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎችና የንግድ ፍቃድ ማረጋገጫን ጨምሮ በርካታ የልደት ካርዶች እና ሌሎች ሰነዶች መያዙን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ መርማሪ ቲም ሀላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ከተማ ኬኔ ገልፀዋል፡፡

ኃላፊው አያይዘው እንደገለጽት ግለሰቦቹ ለህገወጥ ተግባራቸው ይጠቀሙባቸው የነበሩ ኮምፒውተሮችና የተለያዩ ቀለሞች ተይዘዋል፡፡

ሀሰተኛ ሰነዶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊና ፖለቲካዊ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያስከትል ከባድ ወንጀል በመሆኑ ህብረተሰቡ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት የሚሸጡ እና ሀሰተኛ ሰነድ በገንዘብ ገዝተው እራሳቸውን ብቻ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን በመጠቆምና ለህግ አካላት አሳልፎ በመስጠት እችንዲተባበርም ጠይቀዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.