Fana: At a Speed of Life!

በአዳማ ከተማ ለዳያስፖራው የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የምስጋና ዝግጅት እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዳማ ከተማ ለዳያስፖራው የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የምስጋና ዝግጅት እየተከናወነ ነው።
በፕሮግራሙ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ በኩል መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሀገራችሁ በብዙ የህልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባችበት ወቅት ሀገሬን አላስነካም ብላችሁ በተለያየ መልኩ ስትሞግቱና እውነቱን ስትገልጡ ሃገርን መውደድ በተግባር አሳየይታችኋልና እናንተ የኢትዮጵያ አምባሳደር ናችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሰራችሁት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ውጤት አምጥታችሁ ሀገራችሁን አሸናፊ አድርጋችኋል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ እናንተም ተሳክቶላችኋል፣ ኢትዮጵያም ታመሰግናችኋለች ብለዋል።
አሁንም ሀገር በፈለገቻችሁ ጊዜ ጥሪዋን ተቀብላችሁ እዚህ መገኘታችሁ ቀጣይ ስለ ሃገራችሁ በአንዳንድ አለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደሚዘገበው አለመሆኑን የምታጋልጡበት እድል ነው፣ በዚህም ላይ ዘመቻችሁን አጠናክታችሁ እንድትቀጥሉ ሲሉ አክለዋል።
በቆይታችሁ የተጎዱ ወገኖችንና የወደሙ አካባቢዎችን በመመልከት በተለያየ መልኩ ድጋፋችሁን ለወገናችሁ አሳዩ ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግና በሃገር ቤት ያለውን ያልተነካ ሃብት ተገንዝባችሁ በተለያዩ የልማትና የኢንቨስትመንት ስራዎች እንድትዳተፉ ሲሉ አቶ አወሉ አብዲ የርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን መልዕክት ለዳያስፖራው አስተላልፈዋል።
በፍሬህይወት ሰፊው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.