Fana: At a Speed of Life!

በአድዋ ድል የተመሰረተው የአንድነት ተምሳሌትነትን ወጣቱ ሊደግመው እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአድዋ ድል የተመሰረተው የአንድነትና የመተባበር ተምሳሌትነትን ወጣቱ በመተግበር በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግና በማሳካት ሊደግመው እንደሚገባ ተገለጸ።

125ኛው የአድዋ ድል በዓል የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች እና ወጣቶች በድምቀት አክብረዋል።

የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ይታያል ደጀኔ እንደገለጹት፣ የአድዋ ድል በዓል ጀግኖች አርበኞች በመተባበር እና በህብረት ያስገኙት ውጤት ነው።

አሁን ያለው ትውልድም የኢትዮጵያ ብልጽግናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ባለው ጥረት ተሳትፎን በማጎልበት እና የሚጠበቅበትን በመወጣት ድሉን ሊደግመው ይገባልም ሲሉም ተናግረዋል።

የበዓሉ ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን ታሪክ ለተተኪው በማስተዋወቅ ረገድ ብዙ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።

የበዓሉ አከባበርም በስነ ጽሁፍ፣ በትእይንቶች እና በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተካሂዶ ተጠናቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.