Fana: At a Speed of Life!

በአገር አቀፍ ደረጃ አዲስ የኮቪድ-19 ማዕበል መከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገር አቀፍ ደረጃ አዲስ የኮቪድ-19 ማዕበል መከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት አስታውቋል፡፡
ኢንስቲቲዩቱ ሰሞኑን በተከሰተው ጉንፋን መሰል ወረርሽኝ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
በማብራሪያውም ሰሞኑን የተከሰተውን ጉንፋን መሰል ወረርሽኝን ተከትሎ በአንዳንድ ተቋማት በተወሰደ የናሙና ምርመራ ከ59 እስከ 86 በመቶ የሚሆኑት የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው ጠቁሟል፡፡
ኢንስቲቲዩቱ ባለፉት 15 ቀናትም በተለይ በአዲስ አበባ የኮቪድ-19 ስርጭት በስፋት መስተዋሉን ነው የገለጸው፡፡
ወደጤና ተቋማት ሄደው ከተመረመሩት ከ55 ሺህ በላይ ሰዎች ከ25 ሺህ በላይ የሚሆኑት ኮቪድ-19 እንደተገኘባቸው ተመላክቷል፡፡
እንደ አገር ከሁለት ሳምንት በፊት 5 በመቶ የነበረው በኮቪድ19 የመያዝ ምጣኔ አሁን ላይ ወደ 36 በመቶ ከፍ ማለቱም በማብራሪያው ተጠቁሟል፡፡
ዜጎች “የጉንፋን ወረረሽኝ” ከሚለው መዘናጋት ወጥተው የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን በመተግበር ከቫይረሱ እራሱን መጠበቅ እንደሚገባው ኢንስቲቲዩቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተለይም ትምህርት ቤት እና መሰል መስሪያ ቤቶች ጥብቅ የሆነ ኮቪድ መከላከያ ፕሮቶኮል እንዲተገብሩም አሳስቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.