Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ የቤት ለቤት ቅስቀሳ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፋር ከ17ሺህ በላይ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ የቤት ለቤት ቅስቀሳና ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ አቶ መሀመድ ሐመዱ በክልሉ ከ1 ሺህ በላይ ትምህርት ቤቶች ከ166 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብለው ኮሮናን በመከላከል ማስተማር ጀምረዋል።

ይሁን እንጂ በክረምት ወቅት የጎርፍና አንበጣ ክስተት በስፋት በተስተዋለባቸው ገጠራማ አካባቢዎች የሚኖሩ ከ17 ሺህ በላይ የመጀመሪያ ደረጃ መጀመሪያ ሳይክል ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ሳይመለሱ ቀርተዋል ብለዋል ።

የጎርፍና አንበጣ ክስተት ከአርብቶ አደሩ የኑሮ ዘይቤ ጋር ተደምሮ ለተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታ መራቅ ተጠቃሽ ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሚመራ የከፍተኛ አመራሮች አብይ ኮሜቴ ተዋቅሮ እስከ ታችኛው የአስተዳደር እርከን ድረስ በመውረድ ህብረተሰቡን በማነሳሳት ተማሪዎቹን ወደ ትምህርት ገበታ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

የትምህርት ስራ የአንድ ሴክተር ሳይሆን የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ንቁ ተሳትፎ የሚጠይቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከመንግስት መዋቅሩ በተጨማሪ የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም እስከቀበሌ ድረስ አደረጃጀት ያሏቸውን የጤና ኤክስቴንሽንና የግብርና ባለሙያዎችን ባሳተፈ መልኩ የቤት ለቤት ቅስቀሳና የተማሪዎች ምዝገባ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

ከትምህርት ገበታ ውጭ የሚገኙ 17ሺህ በላይ ተማሪዎች በመጭው ሳምንት ውስጥ ወደ ትምህርት እንዲመለሱ እንደሚደረግ ሀላፊው ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.