Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የተገኘ ከ13 ሚሊየን ብር በላይ መያዙን የአውሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ገንዘቡ በኮሪ ወረዳና በጭፍራ ወረዳ በኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ የተገኘ ሲሆን፥ የአውሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አሃዶ መሀመድ እንደገለፁት፥ በክልሉ አውሳ ዞን ሁለት ወረዳዎች ኬላ ላይ በተደረገ ፍተሻ 13 ሚሊየን 53 ሺህ 490 ብር ተይዟል ብለዋል፡፡

በ3 ወራት ውስጥ ብቻ በህገ ወጥ ዝውውር 216 ኩንታል ጨው፣ በሚሌና በዱብቲ ወረዳዎች ቤንዚል ባለ 25 ሊትር 80 ጀሪካን እና ባለ 2 ሊትር ሀይላንድ 280 ሀባ መያዙን መግለጻቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ 24 በርሜል ናፍጣ እና ባለ 25 ሊትር 250 ጀሪካን እንዲሁም 50 ኩንታል ስኳር በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር ተገኝቶ በምርመራ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.